በዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ላይ ያተኮረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አራተኛ ቀን ውሎ

READ THIS IN PDF.

·        አባ ጳውሎስ ጉዳዩ አጀንዳ እንዳይኾን ተቃውመው ነበር
· እትሙ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ ክብር የሚያቃልልና መጥፎ አርኣያነት ያለው መኾኑ በጉባኤው አባላት አጽንዖት ተሰጥቶበታል
·        የጋዜጣው ተጠሪነት ለማን እንደ ኾነ አልታወቀም
·        የጋዜጣው ዋና እና ምክትል አዘጋጆች፣ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና እና ምክትል ሓላፊዎች ዛሬ ቀርበው ይጠየቃሉ
·      የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ንብረት ጉዳይ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳነት ተይዞ ለቋሚ ሲኖዶስ ተመርቶ ነበር
·  ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ ቅ/ሲኖዶስ ፍርድና ውሳኔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 7/2004 ዓ.ም፤ May 15/ 2012)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ በትናንት፣ ግንቦት 6 ቀን 2004 ዓ.ም አራተኛ ቀን ውሎው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በ56ዓመት ቁጥር 125፣ ሚያዝያና ግንቦት 2004 ዓ.ም እትሙ ይዞት በወጣው ርእሰ አንቀጽና ጽሑፍ ዙሪያ ሲነጋገር ውሏል፡፡ የጋዜጣው ጽሑፎች ኾነ ብለው በያዙት ቅን ያይደለ አሳብና ዓላማ (Intents and purposes) ሳቢያ ባጸደቃቸው አጀንዳዎች ዙሪያ የጀመረው ውይይት ሂደት የተስተጓጎለበት ምልአተ ጉባኤው÷ ጉዳዩን በርእስነት ይዞ እንዳይነጋገር ከርእሰ መንበሩ አባ ጳውሎስ ተቃውሞ ገጥሞት እንደ ነበር የጉባኤው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ የዚህም ምክንያቱ ሄዶ ሄዶ የጉዳዩ ሥር ፓትርያርኩ ራሳቸው በመኾናቸው ከተጠያቂነት ለመዳን ሚያደርጉት ጥረት መኾኑ ታምኖበታል፡፡

በምልአተ ጉባኤው እምነት ‹የቤተ ክርስቲያን ልሳን› የኾነው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በርእሰ አንቀጹ “የአባቶች ገበና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲጋለጥ” በሚል ርእስ ያወጣው አቋም፣ በቀዳሚ ገጹ “ቤተ ክርስቲያንንና መንጋዎቿን ከወቅታዊ አደጋ ለመታደግ ከግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚጠበቅ የህልውና ውሳኔ” በሚል ርእስ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ላይ በማተኰር ያተመው ጽሑፍ፡- አባ ጳውሎስ በተመሳሳይ ጉዳዮች ለሚታዩባቸው ግዙፍ ተጠያቂነቶች አንዳች ትኩረት ያልሰጠና ሌሎችን ለማሸማቀቅ በመሣርያነት ያገለገለ፣ ፓትርያርኩ አላግባብ የሚጠቀሙበትን ሥልጣናቸውን የማጠናከር ዝንባሌ ያለው፣ በጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በአጀንዳነት ቀርቦ እልባት እንዲሰጠው በማሰብ ቋሚ ሲኖዶስ የውሳኔ ሐሳብ እንዲያቀርብበት በተመራው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ንብረት ጉዳይ ዕድል ያልሰጠ፣ በአጠቃላይ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ ክብር የሚያቃልልና መጥፎ አርኣያነት የሚታይበት ነው፡፡


ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s