በስዊዲን “አዲስ ቤተ ክርስቲያን" ይከፈታል መባሉን ምዕመናን ተቃወሙ

በስዊዲኗ የስቴክሆልም ከተማ በመጪው እሑድ “ይከፈታል” የተባለ ቤተ ክርስቲያንን አስመልክቶ ምእመናን ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። የተቃውሟቸውን እና ምክንይቱን ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ለሥጋዊ ጥቅምና ለበቀል ብቻ ሲባል ቤተክርስቲያን ”የመክፈት” እንቅስቃሴ፣ በስቶክሆልም ስዊድን
በስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘው የደብረ ሰላም መድኅኔዓለም ቤተክርስቲያን

ውድ አንባቢያን በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ እያልን:- የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የግለሰቦችን ስም እያነሱ ማሳጣት ሳይሆን እያካሄዱት ያሉትን ሥጋዊ እና ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ እኛ የተረዳነውን ያክል ለሌሎች ምእመናን እንዲሁም ለአባቶቻችን ካህናት አሳውቀን በአንድነት ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለማስከበር እንድንነሳ መሆኑን እንድትረዱልን በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነን ”ኢትዮጵያ ዛሬ” በሚባል ድረ ገጽ ላይ አንድ ”መንፈሳዊ” ጥሪ መመልከታችን ነው (አወዛጋቢውን ደብዳቤ ለማንበብ ይጫኑ )። ማስታወቂያው ”ታላቅ የምስራች ለሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ለሆናችሁ በሙሉ” በማለት ይጀምራል:: ከዚያም ወደ ዉስጡ ሲገባ የሚነበብዉ ነገር ለህሊና የሚከብድ፤ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ የሆነ፤ የቤተክርስቲያንን ሥርዓት፣ ከዚያም አልፎ የምእመናንን አንድነት የሚንድ እኩይ ተግባር ሆኖ እናገኘዋለን:: ማስታወቂያው ሲነበብ “… በስቶክሆልም ስዊድን ሶላንቱና ሴንትሩም አካባቢ በዓይነቱ ልዩ የሆነና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና መሠረት የሚመራ፤ በካህናት አባቶች የተመሠረተ፤ ንብረትነቱም ሆነ ባለቤቱ በግልጽ በስቶክሆልም ስዊድን በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ የሆነ ቤተክርስቲያኑ የሚገኝበት የቦታው አቀማመጥ በዓይነ ሕሊናችን ወደ ሀገራችን ታላላቅ የእምነት ገዳማት የሚያስጉዝ በውስጥ አደረጃጀቱ ብቃት ያለዉ… ወዘተ” በማለት ጸሐፊዉ ”በአይነቱ ልዩ የሆነ ቤተክርስቲያን ”እንደሚከፈት” ያትትና በዕለቱ የቅድስት ድንግ ማርያምንየአቡነ ተክለሐይማኖትንና የአቡነ አረጋዊን የቃል ኪዲን ታቦታት አካትቶ የያዘ አዲስ ቤተክርስቲያን የፊታችን ሚያዝያ 21/ 2004 ዓ.ም ወይም እ.ኤ.አ. ኤፕሪሌ 29/ 2012፤ እሁድ በብፁዕ አቡነ ኤያስ ጸሎትና ቡራኬ ተመርቆ ”ይከፈታል” ብሎ ጥሪዉን ያጠናቅቃል::

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Advertisements

3 thoughts on “በስዊዲን “አዲስ ቤተ ክርስቲያን" ይከፈታል መባሉን ምዕመናን ተቃወሙ

  1. Anonymous

    በጣም የሚያሳዝን ዜና ነው በተለይ ምእመናን እኛ ካልተከተልናቸው ምንም ሊያደርጉ ስለማይችሉ እንደነዚ በቤተክርስትያናችን ስም ለሚነግዱ ሰዎች መልስ ሰጥተን ልናሳፍራቸው ይገባል።

    Reply
  2. Anonymous

    ይሄ እሳት በየቦታው እየነደደ ነውና ያለአቅማችሁ በዚህ እሳት ውስጥ እየተማገዳችሁ ያላችሁ ሰዎች ተጠንቀቁ። የቆመ የሚመስለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ /ልክ እየሰራችሁ የሚመስላቸሁ ሰዎች ተዉ/። ቀን ያልፋል፣ ፖለቲከኞች ያልፋሉ፣ ዘረኞች ይሞታሉ፣ ታሪክ ይቀራል፣ ትውልድ ይተካል ቤተክርስቲያን ግን ትኖራለች። ለተራ የግል ጥቅም ብሎ ቤተክርስቲያንን የመክፈል፣ በህብረት እያመለኩ ያሉ የቤተክርስቲያን ልጆችን መለያየት፣ በአይነቁራኛ ማስተያየት፣ እግዚአብሔርን ማሳዘን ለራስም ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ማለፍ ነውና ሁሉም ለራሱ ቢያስብ። እምነት ሳይካድ፣ የቀኖና ጥሰት ሳይኖር ገና ለገና ጊዜ ለሚፈታው ያስተዳደር ችግር ተብሎ። ሐዋርያነት፣ ሰማእትነት yemibalew ክፉውን ማስወገድ፣ ከክፉው ጋር መተናነቅ እንጂ በጥቅም ቀረብኝ ቤተክርስቲያንን መክፈል አይደለም!!!

    Reply

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s