READ THIS ARTICLE IN PDF።
· ገዳሙ በውሳኔው ጸንቷል፤
· “በእኛ በኩል በዚህ ቦታ ላይ ልማት ይሰራ ብሎ መወሰን ፈጽሞ የማይታሰብና የማይታለም ነው። ቦታውም በቅዱሳን መካነ መቃብር የታጠረና የተከለለ ነው” (ገዳሙ)፤
· በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው፤
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 3/2004 ዓ.ም፤ ማርች 12/2012)፦ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ እና ታሪካዊ ገዳማት አንዱ ነው፤ ለግሑሳን(ፍጹማን) ባሕታውያን መሸሸጊያ፣ ለስውራን ቅዱሳን መናኸርያ፣ በብዙ ሺሕ ለሚቆጠሩ መነኮሳት፣ መነኮሳይያት እና መናንያን መጠጊያ፣ ለምእመናኑንም መማፀኛ እና ተስፋ የሆነው የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ለፀለምት ወረዳ መስተዳድር በጻፈው ደብዳቤ ለስብሰባ ወክሎ እንዲልክ የተጠየቀውን መቶ መነኮሳት በጾሙ ምክንያት መላክ እንደማይችል አስታወቀ፡፡
Advertisements