". . .እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ። የሰው ልጅ ሆይ፥ ልብ አድርግ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዓትና ሕግ ሁሉ የምናገርህን ሁሉ በዓይንህ ተመልከት በጆሮህም ስማ የቤቱንም መግቢያ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ። . . ."
ትንቢተ ሕዝቅኤል ፵፬ ፥ ፭
ትንቢተ ሕዝቅኤል ፵፬ ፥ ፭
በሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ልዩ ስሙ Baily Cross Road በሚባል አካባቢ አዲስ የገለልተኛ ክርስቲያናትን በመክፈት አገልግሎት እየሰጠን ነው ብለው የሚሉት ሁለት የአሜሪካን ካሕናት ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ያለ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እውቅና፣ ያለ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ እንደፈለገን በአሜሪካን ሀገር ነው ያለንው ማንም ሊከለክለን አይችልም በሚል ቤተ ክርስቲያን በዘፈቀደ ከፍተው ኑና አስቀድሱ ብለው ባለፈው ቅዳሜ አገልግሎት አለ በማለት ሕዝቡን ሲያዋክቡ ሰንብተዋል። በልዩ ስሙ "ቤሊ ክሮስ ሮድ" በሚባለው አካባቢ የከፈቱት የሚባለው ቤተ ክርስቲያን ከወዲሁ ትልቅ የሕብን ቁጣ ሳያስነሳባቸው እንደማይቀር ተገምቷል።
Advertisements
bertu hulachenm kagonachew nan manem betekerstyanin gabeya ayadergatem