ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ለሁለት አስርተ ዓመታት ወደኖሩበት አሜሪካ በNov. 6, 2013 ለመጀመሪያ ጊዜ በዘመነ ፕትርክናቸው እንደሚመጡ ሰሞኑን ከተለያዩ ዜና ማሰራጫዎች ለመረዳት ችለናል። አመጣጣቸውም በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን የመድኅኒዓለም ቤተክርስቲያን የቅዳሴ ቤት ለማክበር እንደሆነ ለመረዳት ችለናል። እንደሚታወቀው ይህ አጥቢያ በብፁእነታቸው ከተመሰረተ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ” ገለልተኛ “ በሚባል አስተዳደር መቆየቱም ይታወሳል። በዚህ ታሪካዊ የብፁዕነታቸው ጉዞም ይህንን አጥቢያ ወደ እናት ቤተክርስቲያን አስተዳደር እንደሚመልሱት እና በቀጥታ በቅዱስ ሲኖዶስ በሚሾመው ሊቀ ጳጳስ እንደሚተዳደር ይጠበቃል። በዚህም በወሺንግተን ዲሲ አካባቢ በገለልተኛ አስተዳደር ስር የሚኖሩትን አጥቢያዎች ቁጥር በአንድ እንደሚቀንስ እና መልካም እርምጃ እንደሚሆን ይጠበቃል። ሌሎችስ? ምን ይጠብቁ ይሆን? ዛሬም በነ አቶ ወይም ዶክተር እከሌ መመራት ወይስ ቀደምት አባቶቻችን በሰሩልን ሥርዓት?
መልካም ጅምር! ቸር ያሰማን
Go back and learn history what happend even in Egypt. abate yesededal….!!!!!